መቼም በዚህ ዘመን ተጋቢ በዝቷል፡፡ ያው ሰው ሲጋባ ከሁለት ወደ አንድ እንደሚቀየር ሁሉ ጋብቻን ፈቅደውና ወደው፤ አበድኩልሽ፣ ሞትኩልህ ብለው ጎጆ የሚቀልሱ በበዙበት አገር በአንፃሩ ደግሞ ጋብቻን የሚሸሹ ወንደ-ላጤዎችና ሴተ-ላጤዎች ደግሞ ቤት ይቁጠራቸው እንጂ ቆጥሮ ማን ሊዘልቃቸው፡፡ የሚገርመው አንዳንዶቹ ጋብቻን ከመፍራታቸው የተነሳ እስከ 50 ዓመት እንዲያውም ተገንዘው እስከሚወጡ ድረስ እናትና አባታቸው ቤት ማሙሽና ሚሚ ተብለው የሚኖሩ ብዙ አሉ፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ተጋብተው፣ ወልደው ከብደው፣ የወርቅ ኢዮቤልዮ የሚያከብሩ በድሮ ዘመን የተባረከ ትዳር የሰጣቸው በጣት የሚቆጠሩ አባትና እናቶች እንዳሉት ሁሉ፤ በዚህ ዘመን ስንመለከት ግን ተጋብተው በማግስቱ ሁላ የፍርድ ቤት ደጃፍ የማይረግጥ ተጋቢ የለም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል አንዳንዶቹ ከማግባት ይልቅ አርፈው የእናትና አባታቸው ቤት የሚቀመጡት፡፡ ከሚጋቡት ጥንዶች የበለጠ በየጊዜው የሚፋቱ ጥንዶች በዝተዋል፡፡ በእርግጥ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ወጣት ጥንዶች የሉም ማለቴ አይደለም፡፡ ያው በላጤነት የተለመደ ነፃነት እና ትዳር ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ነገሮች ቀድሞ አስቦና ተዘጋጅቶ አለመግባት እንዲሁም ከተጋቡ በኋላ የፍቅር መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ይነገራሉ፡፡ ለማንኛውም “ትዳር ጣፋጭ ነው” እንዳለው ደራሲ በእውቀቱ ጣፋጭ ለማድረግ እንጣር፡፡
"ይህ ጦማር ከምንም ዓይነት የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ጋር ያልተሳሰረና እንዲሁ በሀገራችን ውስጥ ስለሚከሰቱ አንዳንድ ትዝብቶች ብቻ ሂስ ለማቅረብ የተዘጋጀ ነው፡፡"
Wednesday, February 12, 2014
ሶስት ጉልቻ
Subscribe to:
Posts (Atom)
Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture
Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...

-
During a robbery in Guangzhou, China, the bank robber shouted to everyone in the bank: "Don't move. The money belongs to the State....
-
By: Meron Moges-Gerbi, CNN (CNN) -- On a rainy afternoon this spring when President Barack Obama gave the commencement speech a...
-
Egypt and Sudan were holding talks on Wednesday following a decision by Ethiopia to divert the Blue Nile as part of a giant dam projec...