ጎረምሳው ልቡን ያሻፈተችውን ቆንጆ ለሚስትነት ለመጠየቅ አባቷ ቤት ይሄዳል::
......
አባት:- ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ ማስቲካ ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም? ክብረቢስ
ጎረምሳው:-ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ እንዳይሸት ብዬ ነው
አባት:-ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ?
ጎረምሳው:-አዎ ግን አልፎ አልፎ ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ ነው ምጠጣው
አባት:-ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ?!! አታፍርም እንዴ ልጄን ለመጠየቅ ስትመጣ?
ጎረምሳው:-ከእስር ቤት ስወጣ ነው መሄድ የጀመርኩት እንጂ በፊት አልሄድም ነበር
አባት:-የባሰ አታምጣ!!!አንተ ሌባ ልጄን ሰርቀህ ልታበላት ነው እንዴ?
ጎረምሳው:-ሌባ አይደለሁም ሰው ገድዬ ነው እስር ቤት የገባሁት
አባት:-ምን!!!! ነብሰ ገዳይ ነህ?
ጎረምሳው:-አይደለሁም የዛን ቀን በጣም ተናድጄ ስለነበር ነው ሰውየው የኛ ጎረቤት ነበር ልጁን ለማግባት ጠይቄው ከለከለኝ ከዛ ገደልኩት::
አባት:-ና እስቲ ልጄ ና እቀፈኝ ለልጄ እንዳንተ አይነት ጥሩ ባል ነበር ስፈልግ የነበረው