Saturday, August 10, 2013

እስክርቢቶ የዋጠው ልጅ

እናት በቅርቧ ወዳለው ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ስልክ ትደውላለች፡፡

ነርስ፡- “ሀሎ፤ ምን እንርዳዎት?”

እናት፡- “አረ በነፍስ ድረሱልኝ! ልጄ ድፍኑን እስክርቢቶዬን ዋጠብኝ”

ነርስ፡- “እሺ አሁኑኑ እርዳታ የሚሰጥ አምቡላንስ እንልክልዎታለን”

እናት፡- “አምቡላንሱ እስኪመጣ እኔ ምን ላድርግ ታዲያ?”

ነርስ፡- “እስከዚያው በእርሳስ ይፃፉ”

ተወደድኩ ባይ

ልጃገረድ፡- “ታቃለህ አንተን ባየሁ ቁጥር አንድ ትልቅ ሰው ትውስ እንደሚለኝ?”

ተወድጃለሁ ባይ፡- “ውይ ታድዬ ማነው ግን የኔ ቆንጆ?”

ልጃገረድ፡- “ሳይንቲስቱ ቻርለስ ዳርዊን”

ተወድጃለሁ ባይ፡- “እንዴ! እኔ ከርሱ ጋር በመልክ ሆነ በቁመና አልመሳሰል፤ በችሎታ አልመጣጠን፤ እንዴት ሆኖ ነው እሱ ትዝ የሚልሽ የኔ ቆንጆ?”

ልጃገረድ፡- “መጀመሪያ ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው ያለው እሱ አልነበር?”

የሰካራም ነገር

አንዲት ያለአቅሟ ጠጥታ በመጠጥ ድንባዧ የጠፋ ሴት ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ትደውልና “የመኪናዬ ዕቃ በሙሉ ተዘርፏልና ድረሱልኝ” ስትል ታመለክታለች፡፡

ተረኛ ፖሊስም የተሰረቀባትን ዕቃ በቅድሚያ እንድታስመዘግብ ሲጠይቃት “መሪው፣ የእጅ ፍሬኑ፣ ማርሹ፣ ፍሪሲዮን፣ የእግር ፍሬንና ነዳጅ መስጫው ሁሉ እንደሌለ” ተናገረችና ስልኩን ዘጋችው፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ስካሯ ሲበርድላት ወደ ፖሊስ ጣቢያው መልሳ ትደውልና ለፖሊሱ “ይቅርታ ጌታዬ በስህተት በመኪናዬ የኋላ በር ገብቼ ነው እንጂ ሁሉም ነገር ስላለ በቃ ተውት” ብላቸው እርፍ፡፡

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...