Monday, September 23, 2013

አነጋጋሪዋ የአንድ ብር ኖት

clip_image001 

የኢትዮጵያችን የወረቀቱ አንድ ብር ኖት ለየት ያሉ ባህሪያት አሏት፡፡ ከነዚህም ውስጥ አነበሳው ሲያገሳ፣ እረኛው ሲስቅ፣ በሬዎቹ ሲራመዱ፣ ወፎች ሲዘምሩ፣ የአባይ ፏፏቴ በግርማ ሞገሱ ሲፈስ፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ብዙ ድምፆች የሚንጫጩባት ብቸኛ ብር ናት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጣም የሚገርመው ነገር ከአንድ ብር አቅም 13 ጊዜ አንድ ብርነቷን የሚያሳብቁ ፅሁፎች (በፊት ገፅ 7 ጊዜ እና በጀርባ 6 ጊዜ) አሏት፡፡ የፊትአውራሪ የሆነው መቶ ብር እንኳን 10 እሱነቱን የሚገልፁ ፅሁፎች ብቻ ነው ያሉት፡፡ አሁን አንድ ብር ላይ ይህን ያህል የመግለጫ ዝባዝንኬ ማብዛት ምን ይባላል፡፡ ደግነቱ ይህች ብር ወደ ሳንቲም ለመቀየር እየተጓዘች ያለች በመሆኗ ብዙ የሚያጨቃጭቅ ባይሆንም የሆነ ሚስጥር ግን ያላት ይመስላል፡፡ ምናልባት ብ ሰው የሚጠቀምባት በመሆኗ ይሆን? ለማንኛውም ብሔራዊ ባንክን መጠየቁ አይከፋም፡፡

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...