Friday, September 20, 2013

አበባዮሽ…

አበባዮሽ የለም (2X)
መብራቱ አለ? የለም…በየሰፈሩ የለም፥
ውሀውስ አለ? የለም…በየሰፈሩ የለም፥
ኔትዎርኩስ አለ?…በየሰፈሩ፥
መንገዱስ አለ? …በየሰፈሩ፥
ታክሲውስ አለ?… በየሰፈሩ፥
ዋይ ዋይ
ድንቄም ሙዳይ፥ ከብለል በይ (2X)

የራበው አለ? የለም …በየመንደሩ የለም
የከፋው አለ? የለም …በየመንደሩ የለም፥
ለሙት ዓመቱ፥… ችግኝ ትከሉ፣
ዲሽ የሌላቸው…ሰዎች ተጉላሉ፤
ጧት ማታ አዩ፥… ችግኝ ሲተክሉ፥
አበባ ይበቅላል…በየገጠሩ
ውጭም ተልኳል…ተሳክቶ ምርቱ
ዋናው ዶላር ነው….ስንዴ የት አባቱ።
ዋይ ዋይ
የእህል ሙዳይ ከብለል በይ (2X)

አ ብለን መጣን አ ብለን (እያዛጋን)
ሚበላ አለ ብለን።
ኡ ብለን መጣን ኡ ብለን (እየጮህን)
ቀባሪ አለ ብለን።
የእድርተኞች ቤት የለም ካቡ ለካቡ የለም
እንኳን ውሻቸው…. ሞቶአል እባቡ።
ዋይ ዋይ
የእንባ ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)

በሉ ልጆቼ የለም ብሉ በተራ፤ የለም
ቤት ያፈራውን….ደረቅ እንጀራ፤
ተደራጅቼ፣… ወጥ እስክሰራ።
እንኳን ወጥና፣…. የለኝም ኩሽና፣
ስዞር አድራለሁ፣… ቁራሽ ስጠና።
ዋይ ዋይ
የእንጀራ ሙዳይ ከብለል በይ። (2X)

የደመወዝ ለታ የለም የአስቤዛው የለም
ቫቱን አስልቼ፣…. ደላድዬው፣
የ20/80ው፣…. ጎኔን አለው።
ከጎኔ ጎኔ፣…. ኪሴን ኪሴን፤
ወዳጄን ጥሯት፣…. ውሽማዬን፣
እርሷም ከሌለች፣….ኮማሪቷን፣
እንፈፅማለን፣… ራዕይውን፣
እናሳካለን፣… ሌጋሲውን፣
ከዚያም አበሉን… ተሰብስበን።
ዋይ ዋይ
የእጦት ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)

መጣልኝ ብለሽ፣….ብትሞነጭሪ፣
ብትራቀቂ፣….ነሽ አሸባሪ።
ከእጮኛ ጋር …ቡና ብትጠጪ፣
በዚያው እደሪ፣ ቤት እንዳትመጪ
ዋይ ዋይ
የክስ መዝገብ ገለጥ በይ። (2X)

ቅዳሜ መጥቶ …ልዘይረው፣
ጋዜጣ ብሻ፣… የት ላግኘው?
ፉክክር ገባ፥… ሰልፍ ብጠራ፥
ፈቃዴን ነጥቆ፥… እርሱ አሰማራ፥
በሰልፉ ዋዜማ፥… ተንኳኩቶ በሩ፥
ሄጄ ማነው ስል፥… ሰልፍ እንዳትቀሩ፥
ዋይ ዋይ
የጉድ ሙዳይ ኮለል በይ። (2X)

ከብረው ይቆዩ ከብረው
በዓመት አንድ ልጅ ሰድደው፣
በቀን ሶስት ጊዜ በልተው፣
ልጅ ትምህርት ቤት ልከው፣
ከሙሰኛ ጅብ ተርፈው፣
ከበሮት ውሃ ቀድተው፣
መብራት ሳይሰጉ አብርተው፣
ለታክሲ ግፊያ ትተው፣
ቀንቶት 40/60ው፣
ጋዜጣ ሸጠው፣ ገዝተው፣
መሳቀቁንም ትተው፣
ሃሳቦትንም ገልፀው፣
የታሰሩቦት ተፈተው፣
የወደዱትን መርጠው፣
ቻናል ቀያይረው አይተው፣
በሃቅ ነግደው አትርፈው፣
ግብሩን በልኩ ከፍለው፣
ከብረው ይቆዩ ከብረው።

ከብረው ይቆዩ በደግ (2X)
የወለዱት ልጅ ይደግ።
ከብረው ይቆዩ በፏፏ (2X)
የወለዱት ልጅ ይፏፏ።
ይሸታል ጠጅ ጠጅ (2X)
የኢትቪዮጵያ ደጅ።
የሸታል ሽሮ ሽሮ (2X)
የማምዬ ጓሮ።

/ዮሐንስ ሞላ/

Source: http://yohanesml.com/

Tuesday, September 17, 2013

ሌባ የማይገኘው ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲደበቅ ነው


አማርኛ በባህርዳር

ለስራ ጉዳይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወደ ባህርዳር ከተማ ሄጄ ነበር፡፡ ታዲያ ከመካከላችን አንዱ የደቡብ ክልል ተወላጅ በመዲናዋ ከሚገኙ አንድ ጎዳና ላይ “ተቋማት” ተብሎ መፃፍ የነበረበት ቃል “ተቆማት” ተብሎ ተፅፏል፡፡ ለዛውም የአማራ ክልል መዲና በሆነቸው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ፤ የሆነ ቢል ቦርድ ላይ ማለት ነው፡፡ እና ምን ቢል ጥሩ ነው? “ለምንድን ነው እንደዚህ የሚፃፈው እኔ እኮ አባቴ ሳይማር ያስተማረኝና አማርኛን በትውልድ ሳይሆን በትምህርት ያወቅኩ ሰው ነኝ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ መፃፉ ይከነክነኛል፡፡” አለ፡፡ እኛም ገርሞን ተሳሳቅንና “ከደቡብ ክልል መጥተህ እዚህ አማርኛ በተወለደበት ቦታ ኢዲተር መሆን አማረህ” ብለን ቀለድንበት እና በደንብ ተሳሳቅን፡፡ ግን እኮ ይህ ዓይነቱ ስህተት በየቦታው ነው ያለው፡፡ ታላላቅ ዝግጅቶች እንኳን ሲዘጋጁ የሚፃፉ ማስታወቂያዎች፣ ቢል ቦርዶች፣ በራሪ ፅሁፎች ላይ እራሱ ስህተት ይታያል፡፡ የሚገርም እኮ ነው፡፡ ምናልባትም እንግዲህ ይህ ዓይነቱ ስህተት የሚመጣው ፀሃፊው ዲቃላ ፊደል የመፃፍ ችሎታ ስለሌለው ወይም ደግሞ “ዲቃላ” የሚለውን ቃል በመፍራቱ ሊሆን ይችላል፡፡ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው በተለይ ብዙ ሰው የሚያነባቸውን ፅሁፎች በደንብ ትኩረት ሰጥተናቸው አርመን ከልሰን ከጨረስን በኋላ ለተጠቃሚ ብናደርሳቸው ይሻላል ለማለት ያህል ነው፡፡

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...