Tuesday, September 17, 2013

አማርኛ በባህርዳር

ለስራ ጉዳይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወደ ባህርዳር ከተማ ሄጄ ነበር፡፡ ታዲያ ከመካከላችን አንዱ የደቡብ ክልል ተወላጅ በመዲናዋ ከሚገኙ አንድ ጎዳና ላይ “ተቋማት” ተብሎ መፃፍ የነበረበት ቃል “ተቆማት” ተብሎ ተፅፏል፡፡ ለዛውም የአማራ ክልል መዲና በሆነቸው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ፤ የሆነ ቢል ቦርድ ላይ ማለት ነው፡፡ እና ምን ቢል ጥሩ ነው? “ለምንድን ነው እንደዚህ የሚፃፈው እኔ እኮ አባቴ ሳይማር ያስተማረኝና አማርኛን በትውልድ ሳይሆን በትምህርት ያወቅኩ ሰው ነኝ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ መፃፉ ይከነክነኛል፡፡” አለ፡፡ እኛም ገርሞን ተሳሳቅንና “ከደቡብ ክልል መጥተህ እዚህ አማርኛ በተወለደበት ቦታ ኢዲተር መሆን አማረህ” ብለን ቀለድንበት እና በደንብ ተሳሳቅን፡፡ ግን እኮ ይህ ዓይነቱ ስህተት በየቦታው ነው ያለው፡፡ ታላላቅ ዝግጅቶች እንኳን ሲዘጋጁ የሚፃፉ ማስታወቂያዎች፣ ቢል ቦርዶች፣ በራሪ ፅሁፎች ላይ እራሱ ስህተት ይታያል፡፡ የሚገርም እኮ ነው፡፡ ምናልባትም እንግዲህ ይህ ዓይነቱ ስህተት የሚመጣው ፀሃፊው ዲቃላ ፊደል የመፃፍ ችሎታ ስለሌለው ወይም ደግሞ “ዲቃላ” የሚለውን ቃል በመፍራቱ ሊሆን ይችላል፡፡ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው በተለይ ብዙ ሰው የሚያነባቸውን ፅሁፎች በደንብ ትኩረት ሰጥተናቸው አርመን ከልሰን ከጨረስን በኋላ ለተጠቃሚ ብናደርሳቸው ይሻላል ለማለት ያህል ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...