በጣም የሚዋደዱ ባልና ሚስቶች ነበሩ፡፡ እናም ፍቅራቸውን ለተመለከተ ሰው በጣም ያስቀናሉ፡፡
ይህን ሁሉ ዘመን በሰላምና በፍቅር ሲኖሩ ባልየው ለሚስቱ ታማኝ፣ ቤቱን አጠንክሮ የያዘና በፀባዩ የተመሰገነ ነበር፡፡ ታዲያ ከዕለታት
አንድ ቀን ባልዬው ትንሽ ጥፋት ያጠፋና ሚስት ሆዬ ቡራ ከረዩ ትላለች፡፡ የዚህን ጊዜ ባል “ምን ሆነሽ ነው፤ እስከዛሬ ያደረኩትን
መልካም ነገር ዘንግተሽ እንዴት ዛሬ ይህችን ያልረባች ጥፋት አጋነንሻት”
ብሎ ጠየቀ፡፡ የዚህን ጊዜ ሚስት “ምን መሰለህ፤ እስኪ በምሳሌ ልንገርህ፤
አንድ ነጭ ወረቀት ላይ ትንሽ ጥቁር ነጥብ ብትኖር የበለጠ የሚታየው የቱ ይመስልሃል” ብላ ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት፡፡
ባልም “ጥቁር
ነጥቡ” አለ፡፡
እሷም “ይኸውልህ
አለችው፤ ከወረቀቱ ይልቅ ትንሿ ነጥብ ጎልታ እንደታዬችህ ሁሉ ከብዙ ጥሩ ስራህ ይልቅ ይህች ትንሿ መጥፎ ስራ ጎልታ ትታያለች” አለችው ይባላል፡፡
እናም “የወንጀልና የቁርስ ትንሽ የለውም” ብለን እንደምድም፡፡