የአዲስ
አበባ እድሜ ጠገብ አንበሳ አውቶቡስ ድርጅት በቢሾፍቱ ባስ ከተሰራ ወዲህ የማስታወቂያዎች የደራ ገበያ ማሟሟቂያ ሆኗል፡፡ ክፍያ ይኑረው አይኑረው ባላውቅም ብቻ ድሮ የምናውቀው ቀይ በቢጫ ቀለም አንበሳ አውቶቡስ ዛሬ የኢንዶሚ፣ የአንቦ ውሃ እና ሌሎች ማስታወቂያዎች ጠቅላላ አካሉን ሸፍነውት ስንት ቁጥር እንደሆነ ራሱ ለማወቅ ያዳግታል፡፡ እኔማ ሳስበው እኛ ሀገር ውስጥ ስታንዳርድ እና ብራንድ ስም የሚባል ነገር ለምን አይኖርም እላለሁ፡፡ ላልረባ ጥቅም ከድሮ ጀምሮ ስንጠቀምበት ለምደነው የኖርንበትን ልማድ ቀይረው የማስታወቂያ ድርጅት አስመሰሉት እኮ፡፡
ስለሆነም፤ መንግስት ለሀገሪቷ መልካም ስም በማሰብ የማስታወቂያውን መጠን ራሱ በትንሽ ካሬ ሜትር ለክቶ ቢያደርግ ለራሱም ስታንዳርዱን ጠብቆ ለመቆየት እና ተሳፋሪም ከመደናገር ይድናል፡፡