ጅቦች መብታችን ማስከበር አለብን በማለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ መሰረቱ።
ጅቦቹም “ቆይ እኛ በዚህች አገር ስንኖር መድሎ ለምን ይፈጸምብናል? ከአንበሳ እኩል እየታየን አይደለም!” በማለት አቤቱታቸውን ለዳኛው ያቀርባሉ፡፡
ዳኛውም በመገረም “ቆይ በዚህች አገር እናንተ ከአንበሳ የተለየ ምን በደል ደረሰባችሁ? ለአንበሳስ ምን የተለየ እንክብካቤ ተደረገለት?” በማለት ይጠይቃሉ።
ጅቦቹም “የተከበሩ ዳኛ በዚህች አገር ውስጥ በአንበሳ ስም
ስንት ነገሮች ተሰይመዋል። ለምሳሌ ብናይ አንበሳ ባንክ፣
አንበሳ ኢንሹራንስ፣ አንበሳ ሻይ፣ አንበሳ አውቶብስ…… ከጫማ እንኳ ሳይቀር አንበሳ ጫማ አለ። እስኪ በእኛ ስም የተሰየመ ነገር ይጥሩልኝ?” አሏቸው።
በንዴት ዳኛውም በጅብ ስም የተሰየመ ነገር ባለመኖሩ ተገርሞ እውነትም በደል ደርሶባቹሃል ስለዚህ ምን ምን በስማችሁ እንዲሰየምላችሁ ትሻላችሁ በማለት ይጠይቃሉ፡፡
ጅቦቹም ትንሽ አሰላሰሉና ጅብ ማዘጋጃ፣ ጅብ ጉሙሩክ፣ ጅብ ቴሌ ተብሎ እንዲሰየምልን እንፈልጋለን። ክቡር ዳኛ እንዲያው ቅር ካልተሰኙ ምን አለ እናንተስ በእኛ በጅቦች ስም ብትሰየሙ..”ጅብ ዳኛ”..