ለሁለት ተሰብሳቢዎች ማይክሮፎን መጠቀም ምን የሚሉት ስልጣኔ፤ ምን የሚሉት ቅብጠት ነው ወዳጆቼ፡፡
አንደኛ ለጆሮ ጥሩ አይደለም፡፡ ሁለተኛም የመብራት ፍጆታ ይወስዳል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በስብሰባ ብዛት የተነሳ አንድ ሁለት ተሰብሳቢዎች
ብቻ ቢሆኑም ትልቅ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ሰብሳቢው ድምፁን በማይክሮፎን ደብልቆ ሰበሰበ ለመባል ብቻ የሚደረግ ስር የሌለው ተግባር
ነው፡፡ እኔማ አንዳንዴ ሳስበው የኢትዮጵያ ቀሪ ሀብትና ባህል ስብሰባ ብቻ ሆነ እንዴ እላለሁ፡፡ እውነቴን እኮ ነው የምላችሁ ለጥቃቅን
ነገር ሁሉ ስብሰባ፤ ስራ ተዘግቶ፤ ደንበኛ እየተጉላላ፡፡ በተለይ በተለይ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለው ይኼው ነው፡፡
ደግሞ እኮ ከጥንት ጀምሮ ነው፤ በንጉሱ ጊዜም እንደዚሁ ወሬ ሲያሞቁ ይውሉና የህዝቡን ችግር ይዘነጉት ነበር፤ በደርግ ጊዜም ጓድ
ሊቀመንበር በጦር ሜዳም ቢሆን ተናጋሪ በመሆናቸው ብዙ ያወራሉ፤ ይሰበሰባሉ፤ ያሁኑ ይባስ ደግሞ ሁልጊዜ ስብሰባ፡፡ እድገታችን በስብሰባ
ብዛት የሚለካ ከሆነ አላውቅም ብቻ፡፡ እኔ እንደሚገባኝ በጋራ ውሳኔ የሚሻ ጠቃሚ ነገር ሲፈጠር ብቻ ነው ስብሰባ የሚያስፈልገው፡፡
ስለዚህ መቼም ስብሰባ ይጥፋ ብዬ አልሞግትም፤ ይልቁንም በወግና ባግባብ መሆን አለበት ብዬ
ነው የምደመድመው፡፡
No comments:
Post a Comment