Friday, August 23, 2013

"የኛ ሰፈር እብዶች እና ቀልዶች" ከሚባለው የፌስቡክ ገፅ ላይ ሳነብ ያገኘሁት፡፡ እንደሚያዝናና ስለገመትኩ ለናንተም ላካፍላችሁ፡-

ጎረምሳው ልቡን ያሻፈተችውን ቆንጆ ለሚስትነት ለመጠየቅ አባቷ ቤት ይሄዳል::
......
አባት:- ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ ማስቲካ ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም? ክብረቢስ
ጎረምሳው:-ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ እንዳይሸት ብዬ ነው
አባት:-ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ?
ጎረምሳው:-አዎ ግን አልፎ አልፎ ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ ነው ምጠጣው
አባት:-ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ?!! አታፍርም እንዴ ልጄን ለመጠየቅ ስትመጣ?
ጎረምሳው:-ከእስር ቤት ስወጣ ነው መሄድ የጀመርኩት እንጂ በፊት አልሄድም ነበር
አባት:-የባሰ አታምጣ!!!አንተ ሌባ ልጄን ሰርቀህ ልታበላት ነው እንዴ?
ጎረምሳው:-ሌባ አይደለሁም ሰው ገድዬ ነው እስር ቤት የገባሁት
አባት:-ምን!!!! ነብሰ ገዳይ ነህ?
ጎረምሳው:-አይደለሁም የዛን ቀን በጣም ተናድጄ ስለነበር ነው ሰውየው የኛ ጎረቤት ነበር ልጁን ለማግባት ጠይቄው ከለከለኝ ከዛ ገደልኩት::
አባት:-ና እስቲ ልጄ ና እቀፈኝ ለልጄ እንዳንተ አይነት ጥሩ ባል ነበር ስፈልግ የነበረው

ወይ የሰው ነገር

ፍርድቤቱ ጥቅጥቅ ብሎ ሞልቷል፤ ተከሳሹ በሀፍረት አቀርቅሮ ቆሟል፤ ዳኛው ጥቁር ካባቸውን ደርበው ተሰይመዋል፤ ችሎቱ ውስጥ የውጥረት ፀጥታ ሰፍኗል…
ዳኛው ክሱን ማንበብ ጀመሩ
“እንግዲህ የመጀመርያው ክስህ ባለቤትህን በመዶሻ ግንባሯ ላይ ደጋግመህ በመምታት ገለሀታል የሚል ነው…”
በድንገት ከፍርድቤቱ የጀርባ ወንበሮች አካባቢ “ከይሲ! አረመኔ!” የሚል ድምፅ ተሰማ
ዳኛው ክሱን ማንበብ ቀጠሉ
ሁለተኛው ክስ ደሞ የባለቤትህን እናት በመዶሻ በአሰቃቂ ሁኔታ ገለሀል በሚል ነው
አሁንም ከሗላ በኩል “አፈር ብላ! አረመኔ!” የሚል ድምፅ አስተጋባ
ይሄኔ ዳኛው በጣም ተበሳጩና፤ ማነው እንደዚህ ችሎቱን የሚበጠብጠው ፤ እስቲ ወደፊት ተጠጋ! ብለው አስጠሩትና ለምን እነዚህን ነገሮች እንደተናገረ ጠየቁት
ሰውዬውም ዳኛው ፊት ቀርቦ እንዲህ ብሎ መለሰ:-
"አሁን የተከሰሰው ሰውዬ ለ15 አመት ያህል ጎረቤቴ ነበር፤ ባለቤቱን እና አማቹንም አውቃቸዋለሁ ፤ ይሄ ሁሉ አመት ስንኖር ለአንዳንድ ስራዎች ፈልጌ መዶሻ እንዲያውሰኝ ስጠይቀው ሁልጊዜ የለኝም ነበር የሚለኝ … አሁን መዶሻ እያለው እንደከለከለኝ ስለገባኝ ተበሳጭቼ ነው፡፡

Source: www.fb/amanuelhospital

Saturday, August 10, 2013

እስክርቢቶ የዋጠው ልጅ

እናት በቅርቧ ወዳለው ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ስልክ ትደውላለች፡፡

ነርስ፡- “ሀሎ፤ ምን እንርዳዎት?”

እናት፡- “አረ በነፍስ ድረሱልኝ! ልጄ ድፍኑን እስክርቢቶዬን ዋጠብኝ”

ነርስ፡- “እሺ አሁኑኑ እርዳታ የሚሰጥ አምቡላንስ እንልክልዎታለን”

እናት፡- “አምቡላንሱ እስኪመጣ እኔ ምን ላድርግ ታዲያ?”

ነርስ፡- “እስከዚያው በእርሳስ ይፃፉ”

ተወደድኩ ባይ

ልጃገረድ፡- “ታቃለህ አንተን ባየሁ ቁጥር አንድ ትልቅ ሰው ትውስ እንደሚለኝ?”

ተወድጃለሁ ባይ፡- “ውይ ታድዬ ማነው ግን የኔ ቆንጆ?”

ልጃገረድ፡- “ሳይንቲስቱ ቻርለስ ዳርዊን”

ተወድጃለሁ ባይ፡- “እንዴ! እኔ ከርሱ ጋር በመልክ ሆነ በቁመና አልመሳሰል፤ በችሎታ አልመጣጠን፤ እንዴት ሆኖ ነው እሱ ትዝ የሚልሽ የኔ ቆንጆ?”

ልጃገረድ፡- “መጀመሪያ ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው ያለው እሱ አልነበር?”

የሰካራም ነገር

አንዲት ያለአቅሟ ጠጥታ በመጠጥ ድንባዧ የጠፋ ሴት ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ትደውልና “የመኪናዬ ዕቃ በሙሉ ተዘርፏልና ድረሱልኝ” ስትል ታመለክታለች፡፡

ተረኛ ፖሊስም የተሰረቀባትን ዕቃ በቅድሚያ እንድታስመዘግብ ሲጠይቃት “መሪው፣ የእጅ ፍሬኑ፣ ማርሹ፣ ፍሪሲዮን፣ የእግር ፍሬንና ነዳጅ መስጫው ሁሉ እንደሌለ” ተናገረችና ስልኩን ዘጋችው፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ስካሯ ሲበርድላት ወደ ፖሊስ ጣቢያው መልሳ ትደውልና ለፖሊሱ “ይቅርታ ጌታዬ በስህተት በመኪናዬ የኋላ በር ገብቼ ነው እንጂ ሁሉም ነገር ስላለ በቃ ተውት” ብላቸው እርፍ፡፡

Wednesday, July 31, 2013

ሶስት ብርጭቆ…

አንድ ሰውዬ ሁልጊዜ ወደ ቡና ቤት ጎራ ሲል አንድ ዓይነት መጠጥ በሶት የተለያዩ ብርጭቆዎች በማዘዝ ፊት ለፊቱ ደርድሮ በየተራ ከሶስቱም እየተጎነጬ ነው የሚጠጣው፡፡ ታዲያ ይህ ከሰው ለየት ያለ ባህሪው የሚያስገርመው የመጠጥ ቤቱ አስተናጋጅ አንድ ቀን “ይቅርታ ወንድሜ! ሁልጊዜ አንድ ዓይነት መጠጥ በሶስት ብርጭቆ እያዘዝከኝ ሁሉንም የምትጠጣው ግን አንተው ነህ፤ ከዚህ ሁሉ አንዱን ጠጥተህ ስትጨርስ ሌላውን ባመጣልህ አይሻልም?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡

ሰውዬውም “የለም! የለም! አየህ ይህ ትልቅ ምክንያት አለው፤ አንዱ ብርጭቆ የኔ ድርሻ ሲሆን፤ ሁለቱ ግን ለስራ ፊልድ የሄዱ በጣም የምወዳቸው ጓደኞቼ ድርሻ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱን ለማስታወስ ስል ነው በሶስት ብርጭቆ አዝዤ የምጠጣው” ሲል ይመልስለታል፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ይህ ሰውዬ ያለወትሮው ሁለት ብርጭቆ መጠጥ ብቻ ቢያዘው አስተናጋጁ ግራ በመጋባት “ውይ ዛሬ ምነው ሁለት ብቻ አዘዝከኝ? አንዱ ጓደኛህ ሞተ እንዴ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡

ሰውዬውም “የለም የለም ሁለቱም ደህና ናቸው፤ እኔ መጠጥ ስላቆምኩ የራሴን ድርሻ ቀንሼ ነው” ብሎት እርፍ!!

Thursday, July 25, 2013

ለካስ…

ዶክተር ወዳጁን መንገድ ዳር ያገኘ ግቭሮቭ ህመሜን የሚያስታግስልኝን መድሃኒት ቢነግረኝ በማለት፤ “ዶክተር፣ ጉንፋን ሲይዝዎ ምን ያደርጋሉ?” ብሎ ቢጠይቀው፣ “እስላለኋ ወዳጄ” ሲል መለሰለት፡፡ ለካስ እሱም ጋቭሮቭ ኖሯል፡፡

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...