Wednesday, February 12, 2014

ሶስት ጉልቻ

መቼም በዚህ ዘመን ተጋቢ በዝቷል፡፡ ያው ሰው ሲጋባ ከሁለት ወደ አንድ እንደሚቀየር ሁሉ ጋብቻን ፈቅደውና ወደው፤ አበድኩልሽ፣ ሞትኩልህ ብለው ጎጆ የሚቀልሱ በበዙበት አገር በአንፃሩ ደግሞ ጋብቻን የሚሸሹ ወንደ-ላጤዎችና ሴተ-ላጤዎች ደግሞ ቤት ይቁጠራቸው እንጂ ቆጥሮ ማን ሊዘልቃቸው፡፡ የሚገርመው አንዳንዶቹ ጋብቻን ከመፍራታቸው የተነሳ እስከ 50 ዓመት እንዲያውም ተገንዘው እስከሚወጡ ድረስ እናትና አባታቸው ቤት ማሙሽና ሚሚ ተብለው የሚኖሩ ብዙ አሉ፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ተጋብተው፣ ወልደው ከብደው፣ የወርቅ ኢዮቤልዮ የሚያከብሩ በድሮ ዘመን የተባረከ ትዳር የሰጣቸው በጣት የሚቆጠሩ አባትና እናቶች እንዳሉት ሁሉ፤ በዚህ ዘመን ስንመለከት ግን ተጋብተው በማግስቱ ሁላ የፍርድ ቤት ደጃፍ የማይረግጥ ተጋቢ የለም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል አንዳንዶቹ ከማግባት ይልቅ አርፈው የእናትና አባታቸው ቤት የሚቀመጡት፡፡ ከሚጋቡት ጥንዶች የበለጠ በየጊዜው የሚፋቱ ጥንዶች በዝተዋል፡፡ በእርግጥ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ወጣት ጥንዶች የሉም ማለቴ አይደለም፡፡ ያው በላጤነት የተለመደ ነፃነት እና ትዳር ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ነገሮች ቀድሞ አስቦና ተዘጋጅቶ አለመግባት እንዲሁም ከተጋቡ በኋላ የፍቅር መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ይነገራሉ፡፡ ለማንኛውም “ትዳር ጣፋጭ ነው” እንዳለው ደራሲ በእውቀቱ ጣፋጭ ለማድረግ እንጣር፡፡1509313_799126630117386_1591916346_n

Friday, December 20, 2013

...
መቼም ቆንጆ ሲታይ ለማድነቅ “ፐ” አይደል የሚባለው?
“ፐ” ብሎ ጀምሮ በ “ፖ” ከሆነ የህይወት ቋጠሮ፣
ለምን ሌላው ከ “ሀ” እስከ “ፈ” ብቻ ቆጥሮ፣
ነፍሱን አይታደግም ለዘንድሮ፡፡
=============
©ካሳሁን ከበደ፤ 2000 ዓ.ም.

Wednesday, December 18, 2013

የማስታወቂያ ባህላችን

ይህ የምታዩት ምስል የምሁሮች መፍለቂያ ከሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዋናው በር አጠገብ ያነሳሁት ነው፡፡ በትልቁ “ማንኛውንም ማስታወቂያ መለጠፍ ክልክል ነው” የሚል ማስታወቂያ ቢለጠፍም ብዙ ማስታወቂያዎች የሚታዩ ሲሆን፤ ከዚህም ብዙውን ቦታ የሚሸፍኑት በራሱ በዩኒቨርሲቲው የተለጠፉ ናቸው፡፡ በእርግጥ በራሱ አጥር ላይ መለጠፍ መብቱ ቢሆንም፤ አለጣጠፉ ግን በጣም ያስጠላል፡፡ በአግባቡ ቦርድ ነገር ሰቅሎ መለጠፍ ሲቻል፤ በኮላ በማጣበቅ አካባቢ እያቆሸሹ ልክ በየመንገዱ እንደሚለጠፉት ማስታወቂያዎች ነው እየተደረገ ያለው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንደዚህ ሲደረግ አይቶ በየመንገዱ የሚለጥፈው ሰው ታዲያ ለምን ይወቀሳል፡፡Image013

Saturday, December 14, 2013

ደደብ ነህ!

ልጅቷ፡ ልትረዳኝ ትችላለህ?

ልጁ፡ በትክክል፤ ምንድን ነው?

ልጅቷ፡ የሆነ ልጅ እንዲወደኝ እፈልጋለሁ

ልጁ፡ ማን ነው?

ልጅቷ፡ ልነግርህ አልችልም

ልጁ፡ እሺ፤ ለምን እንደምትወጂው አትነግሪውም?

ልጅቷ፡ እንዴት ብዬ?

ልጁ፡ በይዋ

ልጅቷ፡ እወድሃለሁ

ልጁ፡ አዎ፤ እንደዛ ማለት ነው

ልጅቷ፡ ደደብ ነህ

Wednesday, December 4, 2013

የሰሞኑ የቦሌ ትዕይንት

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ህገ-ወጥ የተባሉ እህት ወንድሞቻችን ከሃገር ውጡ ተብለው ወደ እናት ሃገራቸው መመለስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የድሮው አውሮፕላን ማረፊያ ጉምሩክ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በሰው ብዛት ተጥለቅልቋል፡፡ ለካ ሳውዲ አረቢያን ክልል 15 አድርገናት ነበር፡፡ አይ ይህች እንጀራ፤ ያልፍልናል ብለው ሄደው በግፍ የተባረሩ ወገኖቻችን ናቸው፡፡ በሳውዲ ብዙ ዘመናት ቢያስቆጥሩም የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ወገኖች ሶስት እና አራት ልጆች ወልደው መቀመጣቸው ግን ገርሞኛል፡፡ በጣም ያሳዝናል ህፃናት ልጆች ይዘው የሚመጡት እኮ ብዙ ናቸው፡፡ ፈቃድ ሳይኖራቸው እንዴት ነው ወልደው ልጅ የሚያሰቃዩት? እርግጥ ነው ይህን ያህል ዓመታት ሲቆዩ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፤ ለምን ተዋለዱ ብዬ አልጠይቅም፡፡ ግን የሰው ሃገር ውስጥ ሲኖር ከኋላ ለሚመጡት ፍጥረቶች ደህንነት ኃላፊነት መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እዛ የታሰሩበት ቦታ ሁሉ የሚበላ የሚቀመስ ሲያጡ ያማቸዋል፤ ከዛ የከፋም ነገር ሊፈጠር ይችላል፡፡ በእርግጥ ድንገተኛ ዱብ እዳ ስለሆነ ከሆነ በኋላ ነው ችግሩ የተከሰተው፡፡

እኔን ግን ከዚህ የበለጠ ግርም ያለኝ ነገር ባዕዳን አባረዋቸው ሃገር አለን ብለው በገዛ ሃገራቸው እዚሁ የሚያርፉበት ድንኳን አካባቢ ኢትዮጵያውያን ነን የሚሉ ወገኖች ከ30 ብር በማይበልጥ ዋጋ የሚሸጠውን ሲም ካርድ በ60 ብር ሲቸበችቡላቸው ነበር፡፡ እኛ ራስ በራሳችን ካልተዛዘንን የሌላ ሃገር ሰው እንዴት ነው የሚያዝንልን? እናም የድሮው መተሳሰባችን ይቀጥል እላለሁ፡፡

የስብሰባ ትዝብት 2

የሆነ ስብሰባ ተሳትፌ ነበር እና ፅሁፍ አቅራቢው መድረክ ላይ አይኑን ላፕ ቶፕ ላይ ተክሎ በፕሮጀክተሩ ለእኛ እያሳየ ይገኛል፡፡ ካሜራ ማኑ ካሜራውን ብልጭ ሲያደርግ ይደነግጥና ንግግሩን አቋርጦ አይኑን ወደ ካሜራ ማኑ ያዞራል፡፡ ከልማድም ልማድ አለ፤ እንዲህ ዓይነት ልማድ ግን አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ መቼም ከህዝብ ፊት ሆኖ መድረክ መምራትን የመሰለ ታላቅ ጥበብ የለም፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ዓይን እሱ ጋ ነዋ የሚያፈጠው፤ አፍጥጦም አይቀርም የሆነች እንከን ካስተዋለ ሂስ እና አቃቂር ማውጣቱ አይቀርም፡፡ ግን የዚህ ሰውዬ ሁኔታ ከሁሉም የተለየ ነው፤ አንዴ ብቻ አይደለም ፅሁፉ እስከሚያልቅ ድረስ እኮ ነው፡፡ እናም ጠረጠርኩ “ምናልባት ይህ ሰውዬ ጦር ሜዳ ያሳለፈ ይሆን እንዴ? አልያም ደግሞ አንድ ቤተሰቡን በመብረቅ አጥቷል፡፡” እሱማ በህይወት አለ፡፡

Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture

Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...