አማኑኤል ሆስፒታል ከሚባል የፌስቡክ ገፅ ላይ ከታች የተለጠፈውን ምስል ሳየው እኔንም የሚኮረኩረኝ ጉዳይ ስለሆነ ለእናንተም ለማካፈል ወደድኩ፡፡ መቼም ቴሌ ሰው ከሰው ለማቆራረጥ እንጂ ለማገናኘት እየሰራ አይደለም፡፡ እንዲያውም እንደኔ እንደኔ በቴክኖሎጂና መገናኛ ሚኒስቴር ስር ከሚሆን ማቆራረጥ የሚለውን ቃል ለመጠቀም ሲባል ተቋራጭ ድርጅቶች ውስጥ ቢገባ ይሻላል፡፡ ተቋራጭ የሚለው ቃል ኮንትራክተሮችን እንደሚመለከት ባውቅም ሌላ ቃል ላገኝ ስላልቻልኩ ነው፡፡ የቴሌ ኃላፊዎች ሁልጊዜ በተጠየቁ ቁጥር ከ6 ወር በኋላ ይስተካከላል፤ የምትል መልስ አለቻቸው፡፡ ነገር ግን እስካሁን ስንት 6 ወራቶች አለፉ፤ ስራውም አልተሰራም፤ እኛም ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር መቆራረጣችን ቀጥሏል፤ እስኪ የሚቻል ከሆነ የቤት ስልክ ከነገመዱ ይዞ መዞር መሞከሩ ሳይሻል አይቀርም፡፡
"ይህ ጦማር ከምንም ዓይነት የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ጋር ያልተሳሰረና እንዲሁ በሀገራችን ውስጥ ስለሚከሰቱ አንዳንድ ትዝብቶች ብቻ ሂስ ለማቅረብ የተዘጋጀ ነው፡፡"
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture
Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...

-
የ11ኛው ዙር አጠቃላይ የአዲስ አበባ 20_80 ኮንዶሚኒየም ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር ለማየት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ https://drive.google.com/file/d/0B7AnIIjHSJxNVEpqc1V4NXVtMz...
-
ጅቦች መብታችን ማስከበር አለብን በማለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ መሰረቱ። ጅቦቹም “ቆይ እኛ በዚህች አገር ስንኖር መድሎ ለምን ይፈጸምብናል? ከአንበሳ እኩል እየታየን አይደለም!” በማለት አቤቱታቸውን ለዳኛው ያቀርባሉ፡፡ ...
-
ይህ የምታዩት ምስል የምሁሮች መፍለቂያ ከሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዋናው በር አጠገብ ያነሳሁት ነው፡፡ በትልቁ “ማንኛውንም ማስታወቂያ መለጠፍ ክልክል ነው” የሚል ማስታወቂያ ቢለጠፍም ብዙ ማስታወቂ...
No comments:
Post a Comment