"ይህ ጦማር ከምንም ዓይነት የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ጋር ያልተሳሰረና እንዲሁ በሀገራችን ውስጥ ስለሚከሰቱ አንዳንድ ትዝብቶች ብቻ ሂስ ለማቅረብ የተዘጋጀ ነው፡፡"
Tuesday, September 17, 2013
አማርኛ በባህርዳር
ለስራ ጉዳይ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ወደ ባህርዳር ከተማ ሄጄ ነበር፡፡ ታዲያ ከመካከላችን አንዱ የደቡብ ክልል ተወላጅ በመዲናዋ ከሚገኙ አንድ ጎዳና ላይ “ተቋማት” ተብሎ መፃፍ የነበረበት ቃል “ተቆማት” ተብሎ ተፅፏል፡፡ ለዛውም የአማራ ክልል መዲና በሆነቸው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ፤ የሆነ ቢል ቦርድ ላይ ማለት ነው፡፡ እና ምን ቢል ጥሩ ነው? “ለምንድን ነው እንደዚህ የሚፃፈው እኔ እኮ አባቴ ሳይማር ያስተማረኝና አማርኛን በትውልድ ሳይሆን በትምህርት ያወቅኩ ሰው ነኝ፡፡ ስለዚህ እንደዚህ መፃፉ ይከነክነኛል፡፡” አለ፡፡ እኛም ገርሞን ተሳሳቅንና “ከደቡብ ክልል መጥተህ እዚህ አማርኛ በተወለደበት ቦታ ኢዲተር መሆን አማረህ” ብለን ቀለድንበት እና በደንብ ተሳሳቅን፡፡ ግን እኮ ይህ ዓይነቱ ስህተት በየቦታው ነው ያለው፡፡ ታላላቅ ዝግጅቶች እንኳን ሲዘጋጁ የሚፃፉ ማስታወቂያዎች፣ ቢል ቦርዶች፣ በራሪ ፅሁፎች ላይ እራሱ ስህተት ይታያል፡፡ የሚገርም እኮ ነው፡፡ ምናልባትም እንግዲህ ይህ ዓይነቱ ስህተት የሚመጣው ፀሃፊው ዲቃላ ፊደል የመፃፍ ችሎታ ስለሌለው ወይም ደግሞ “ዲቃላ” የሚለውን ቃል በመፍራቱ ሊሆን ይችላል፡፡ እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው በተለይ ብዙ ሰው የሚያነባቸውን ፅሁፎች በደንብ ትኩረት ሰጥተናቸው አርመን ከልሰን ከጨረስን በኋላ ለተጠቃሚ ብናደርሳቸው ይሻላል ለማለት ያህል ነው፡፡
Friday, August 23, 2013
ጎረምሳው ልቡን ያሻፈተችውን ቆንጆ ለሚስትነት ለመጠየቅ አባቷ ቤት ይሄዳል::
......
አባት:- ልጄን ለጋብቻ ልትጠይቅ መጥተህ በአጠገቤ ማስቲካ ታኝካለህ ትንሽ እንኳን አታፍርም? ክብረቢስ
ጎረምሳው:-ይቅርታ ጌታዬ ስለጠጣው አፌ እንዳይሸት ብዬ ነው
አባት:-ጭራሽ መጠጥም ትጠጣለህ?
ጎረምሳው:-አዎ ግን አልፎ አልፎ ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ ነው ምጠጣው
አባት:-ናይት ክለብ ስሄድ ብቻ?!! አታፍርም እንዴ ልጄን ለመጠየቅ ስትመጣ?
ጎረምሳው:-ከእስር ቤት ስወጣ ነው መሄድ የጀመርኩት እንጂ በፊት አልሄድም ነበር
አባት:-የባሰ አታምጣ!!!አንተ ሌባ ልጄን ሰርቀህ ልታበላት ነው እንዴ?
ጎረምሳው:-ሌባ አይደለሁም ሰው ገድዬ ነው እስር ቤት የገባሁት
አባት:-ምን!!!! ነብሰ ገዳይ ነህ?
ጎረምሳው:-አይደለሁም የዛን ቀን በጣም ተናድጄ ስለነበር ነው ሰውየው የኛ ጎረቤት ነበር ልጁን ለማግባት ጠይቄው ከለከለኝ ከዛ ገደልኩት::
አባት:-ና እስቲ ልጄ ና እቀፈኝ ለልጄ እንዳንተ አይነት ጥሩ ባል ነበር ስፈልግ የነበረው
ወይ የሰው ነገር
ፍርድቤቱ ጥቅጥቅ ብሎ ሞልቷል፤ ተከሳሹ በሀፍረት አቀርቅሮ ቆሟል፤ ዳኛው ጥቁር ካባቸውን ደርበው ተሰይመዋል፤ ችሎቱ ውስጥ የውጥረት ፀጥታ ሰፍኗል…
ዳኛው ክሱን ማንበብ ጀመሩ
“እንግዲህ የመጀመርያው ክስህ ባለቤትህን በመዶሻ ግንባሯ ላይ ደጋግመህ በመምታት ገለሀታል የሚል ነው…”
በድንገት ከፍርድቤቱ የጀርባ ወንበሮች አካባቢ “ከይሲ! አረመኔ!” የሚል ድምፅ ተሰማ
ዳኛው ክሱን ማንበብ ቀጠሉ
ሁለተኛው ክስ ደሞ የባለቤትህን እናት በመዶሻ በአሰቃቂ ሁኔታ ገለሀል በሚል ነው
አሁንም ከሗላ በኩል “አፈር ብላ! አረመኔ!” የሚል ድምፅ አስተጋባ
ይሄኔ ዳኛው በጣም ተበሳጩና፤ ማነው እንደዚህ ችሎቱን የሚበጠብጠው ፤ እስቲ ወደፊት ተጠጋ! ብለው አስጠሩትና ለምን እነዚህን ነገሮች እንደተናገረ ጠየቁት
ሰውዬውም ዳኛው ፊት ቀርቦ እንዲህ ብሎ መለሰ:-
"አሁን የተከሰሰው ሰውዬ ለ15 አመት ያህል ጎረቤቴ ነበር፤ ባለቤቱን እና አማቹንም አውቃቸዋለሁ ፤ ይሄ ሁሉ አመት ስንኖር ለአንዳንድ ስራዎች ፈልጌ መዶሻ እንዲያውሰኝ ስጠይቀው ሁልጊዜ የለኝም ነበር የሚለኝ … አሁን መዶሻ እያለው እንደከለከለኝ ስለገባኝ ተበሳጭቼ ነው፡፡
Source: www.fb/amanuelhospital
Saturday, August 10, 2013
እስክርቢቶ የዋጠው ልጅ
እናት በቅርቧ ወዳለው ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ስልክ ትደውላለች፡፡
ነርስ፡- “ሀሎ፤ ምን እንርዳዎት?”
እናት፡- “አረ በነፍስ ድረሱልኝ! ልጄ ድፍኑን እስክርቢቶዬን ዋጠብኝ”
ነርስ፡- “እሺ አሁኑኑ እርዳታ የሚሰጥ አምቡላንስ እንልክልዎታለን”
እናት፡- “አምቡላንሱ እስኪመጣ እኔ ምን ላድርግ ታዲያ?”
ነርስ፡- “እስከዚያው በእርሳስ ይፃፉ”
ተወደድኩ ባይ
ልጃገረድ፡- “ታቃለህ አንተን ባየሁ ቁጥር አንድ ትልቅ ሰው ትውስ እንደሚለኝ?”
ተወድጃለሁ ባይ፡- “ውይ ታድዬ ማነው ግን የኔ ቆንጆ?”
ልጃገረድ፡- “ሳይንቲስቱ ቻርለስ ዳርዊን”
ተወድጃለሁ ባይ፡- “እንዴ! እኔ ከርሱ ጋር በመልክ ሆነ በቁመና አልመሳሰል፤ በችሎታ አልመጣጠን፤ እንዴት ሆኖ ነው እሱ ትዝ የሚልሽ የኔ ቆንጆ?”
ልጃገረድ፡- “መጀመሪያ ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው ያለው እሱ አልነበር?”
የሰካራም ነገር
አንዲት ያለአቅሟ ጠጥታ በመጠጥ ድንባዧ የጠፋ ሴት ፖሊስ ጣቢያ ስልክ ትደውልና “የመኪናዬ ዕቃ በሙሉ ተዘርፏልና ድረሱልኝ” ስትል ታመለክታለች፡፡
ተረኛ ፖሊስም የተሰረቀባትን ዕቃ በቅድሚያ እንድታስመዘግብ ሲጠይቃት “መሪው፣ የእጅ ፍሬኑ፣ ማርሹ፣ ፍሪሲዮን፣ የእግር ፍሬንና ነዳጅ መስጫው ሁሉ እንደሌለ” ተናገረችና ስልኩን ዘጋችው፡፡
ከደቂቃዎች በኋላ ሴትየዋ ትንሽ ስካሯ ሲበርድላት ወደ ፖሊስ ጣቢያው መልሳ ትደውልና ለፖሊሱ “ይቅርታ ጌታዬ በስህተት በመኪናዬ የኋላ በር ገብቼ ነው እንጂ ሁሉም ነገር ስላለ በቃ ተውት” ብላቸው እርፍ፡፡
Ethiopian Overlooked and Underutilized Sector - Agriculture
Agriculture is the prominent sector of Ethiopia which millions of lives depend on for centuries. The share still stands high compared ...
-
13th round 20/80 & 2nd round 40/60 Addis Ababa condominium winners list. የ20/80 13ኛው ዙር እና የ40/60 2ኛው ዙር የአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የወጣላቸው ...
-
የ11ኛው ዙር አጠቃላይ የአዲስ አበባ 20_80 ኮንዶሚኒየም ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር ለማየት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ https://drive.google.com/file/d/0B7AnIIjHSJxNVEpqc1V4NXVtMz...
-
By Julia Brakel Laptops and tablets are in everyday use as much in Addis Ababa as elsewhere on the African continent, with the city’s cafes...
